ሓዱሽ ርእቶ ይሃቡ

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ጉባዔ በመቐለ ከተማ ሊካሄድ ነው

ታህሳስ 2/2011(ድምፂ ወያነ) የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ሚና እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ለማድረስ በሚቻልበት ጉዳይ የሚመክር መሆኑን አስታወቀ።

ጉባዔው “የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ በመቐለ ከተማ ከታህሳስ 7 እስከ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።

በጉባዔው 700 አባላት ተሳታፊ ሲሆኑ 620ዎቹ በድምጽ የሚሳተፉ እንደሆኑ እና ሴት ሚኒስትሮችን ጨምሮ ከተለያዩ አደረጃጀቶች የሚሳተፉ ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙ ተገልፇል።